አምላክ ሆይ! ብርክት በሆነች በድንግል ማርያም በኩል ለቅዱሱ ካህን ጆሴማርያ መጠንየለሽ ፀጋን ቸርከው። ኦፑስ ዴን ይመሰርት ዘንድም ፍጹም ታማኝ አገልጋይህ አድረገህ መረጥከው። እሱም ክርስትያኖች እለት በእለት በረከትን እና ቅድስናን ይጎናጸፉ ዘንድ ኦፑስ ዴን መሰረተ። እነሆ እኔም ለሱ የሰጠኸውን በረከት ታድለኝ ዘንድ፣ በሰጠኸኝም ፀጋ ሕይወቴን ላንተ ያለኝን ፍቅር በማሳየት እና ብፁዕ አባታችንን፣ ቤተክርስቲያንን እና መላውን የሰው ዘር በንፁሕ ልቦና በደስታ በማገልገል እንድመራው እርዳኝ። (የሚፈልጉትን ልመና ወይም ጸሎት አዚህ ጋር ይበሉ).........ጸሎት ልመናዬን ትሰማ ዘንድ ቅዱስ ጆሴማርያን አማላጅ አድርጌ እጠይቃለሁ። አሜን። ቀጥሎ የሚከተሉትን ጸሎታት ይበሉ - አባታችን ሆይ......፣ሰላም ላንቺ ይሁን.....፣ ክብር ምስጋና......።
St. Josemaria Prayercard - Amharic (with audio)
St. Josemaria Prayercard - Amharic
Printed | document generated automatically from https://opusdei.org/en-ke/article/st-josemaria-prayercard-amharic/ (09/24/2024)